(መስከረም 14/2019 ዓ.ም ፤አሶሳ )የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም ሰራተኞች በዘንድሮው ክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ ለመደገፍ ከደሞዛቸው ላይ 30% ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል ///*
በክረምት በጎ ፍቃድ ሥራን በተመለከተ ሰራተኞች በጉዳዩ ዙሪያ እንዲወያዩ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ አጄሊ ሙሣ የውይይት መድረኩን ለሰራተኞች ክፍት ያደረጉ ሲሆን በዚሁም በዘንድሮው በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ ተቋማችን በመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባር ለአቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት ፣የቤት ግንባታና ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል ።
በጉዳዩ ዙሪያ ለሰራተኞች በተደረገው ውይይትና ግንዛቤ መሠረት ስለ በጎ ሥራ አስፈላጊነት ግንዛቤ የወሰዱ ሰራተኞች የበጎ ሥራ ተግባር የሚበረታታና አቅም የሌላቸውን ወገኖች መደገፍ አሰፈላጊና ሰብዓዊነት በመሆኑ ከሚያገኙት ደሞዛቸው ላይ በሦስት ወር ልዩነት ውስጥ ተቆራጭ የሚሆን 30% ድጋፍ ለማድረግ በገዛ ፍቃዳቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግሯል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com









