ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር በንቃትና በትጋት እንዲፈፀም ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ሲመሩና ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮችና አሁን ተቋሙን እየመሩ ያሉ የተቋሙ ኃላፊዎችና ማኔጀመንት አባላት አሁናዊ የመንግሥት አገልግሎትና አሰተዳደር ሪፎርም ዙሪያ በተዘጋጀ ስነድ ላይ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል /////////////****
በውይይት ማስጀመሪያ መድረክ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ አጃሊ ሙሣ ጥሪ ለተደረገላቸው የቀድሞ የተቋሙ ቁልፍ ባለሚና እና ባለድርሻ አካላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ ለባለድርሻ አካላት ገለፃ አድረገዋል ።
አቶ አጀሊ በመግለጫቸው እንዳሉት ተቋማችን ባለፉት 28 ዓመታት በብዙ ባለድርሻ አካላት ጥረት በርካታ ውጣውረዶችን ተሻግሮ ሀገራዊና ክልል አቀፍ የሪፎርም ፕሮግራሞችን ፣ስትራቴጂዎችን ፣የትኩረት አቅጣጫዎችን ሲፈጽም እንደነበር ተናግሯል ።
በዚህ መሠረት ለተቋሙ በተልዕኮ የተሰጠውን የማማከር ፣ጥናትና ምርምር የማካሄድ ፣ሥልጠና የመስጠትና የማስተባበር አገልግሎቶችን በየደረጃው ለሚገኙ የሲቪል ሰርቨስ ተቋማት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጀቶች ሲሰጥ የነበረና እየሰጠ የሚገኝ የክልሉ ስልጠና ማዕከል መሆኑን አውስተዋል ።
ለዚህም ለተመዘገቡ የረጅም ዓመታት ስኬቶች የክልላችን መንግሥት ፣ በተለያዩ ጊዜያት ተቋሙን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በኃላፊነት የመሩና ያገለገሉ አመራሮች ፣ባለሚና እና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የአጎራባች ቀበሌ ሕዝብ ከምስረታው እሰከ ዛሬ ድረስ የማይተካ ዋጋ እንዲከፈልበት በእጅጉ የሚደነቅ እና ከፍተኛ ቦታ የሚሰጥ መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል ።
በመጨረሻም የዛሬውን የውይይት መድረክ እንዲካሄድ ያስፈለገበት ምክንያት የተቋሙ የባለሚና እና ቁልፍ ባለድረሻ አካላት ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ አሁን ላለበት ደረጃ የነበረበትን ሁኔታ ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉና ለወደፊቱ ግብዓት ለመውሰድ በመሆኑ ከአሁናዊ የመንግሥት አገልግሎትና አሰተዳደር ሪፎርም ፖሊሲ አኳያ ተቋማችን ከተገባደደው የሥራ ዘመን ጀምሮ የዝግጁነት ሰልጣኝ ወይም አዲስ ተቀጣሪ እና ነባር የመንግስት ሰራተኞችን ባህሪያዊና ቴክኒካል ብቃት የመመዘን እና መብቃታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ተሰጥቶት “የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም “በሚል መጠሪያ በደንብ ቁጥር 178/2017 እንደገና ተሻሽሎ በአዲስ መቋቋሙን ጠቅሶ ገልጸዋል ።
በመሆኑም ነባሩ የመንግሥት ሰራተኛ በተሟላ የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ሥርዐት እና የብቃት ክፍተትን በሚሞላ የሥልጠና ሂደት አልፎ የተሰማራ ስላልነበረ ፣ በሥራ ላይ እያሉ የብቃት ደረጃቸውን በጥናት እንዲለዩና ክፍተት ያለባቸው እንዲያሟሉ የሚደረግበት ፣ በመንግሥት መስሪያ ቤት የሚቀጠሩ አዳዲስ ሰራተኞችም ብቃታቸው ተረጋግጦ እንዲቀጠሩ ፣ እንዲሁም ብቃታቸው የተረጋገጠላቸው ደግሞ በብቃታቸው መሠራት የሚችሉበት ሪፎርም እውን የማድረግ ተጨማሪ ሥልጣን ተሰጥቷል ።
ይህንን የመንግስት አገልግሎት እና አሰተዳደር ሪፎርም ተልዕኮ ከግቡ ለማድረስ ተቋሙ የሚገኝበትን ነባራዊና አሁናዊ ሁኔታ በባለሚና አካላት ውይይት መለየትና የጋራ ምክር ሀሳብ ማስቀመጥ ወሳኝ የዝግጅት ምዕራፍ መሆኑን ገልጿል ።










