(ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም በመተከል ዞን በፓዊ ወረዳ 02 ቀበሌ የአንድ አቅመ ደካማ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሥራ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል*////////////////
በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ንግግር ያደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ አሰፋ፥ በወረዳው በሁሉም መስኮች እየተከናወኑ ያሉ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።
በመሆኑም በዛሬው ዕለት በክልሉ ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም የተጀመረው የአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት ግንባታ ተግባር የመደገፍና የመተሳሰብ ባህልን የሚያጠናክር ከመሆኑም ባሻገር፣ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሻል ተግባር በመሆኑ በአግባቡ እንዲከናወን አስተዳደር ም/ቤቱ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በክልሉ ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም የህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፍዬ አቡኖ በበኩላቸው፥ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሥራው እስከ መስከረም መጨረሻ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ርክክብ እንደሚደረግ የገለፁ ሲሆን፥ በቀጣይም ለአቅመ ደከሞች ማዕድ የማጋራትና ኢኮኖሚያዊ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግ ጭምር ገልፀዋል።
መረጃው ፦በመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ድረ -ገፅ የተወሰደ ነው ።





