በተቋማችን የሠልጣኞች የምኝታ አገልግሎት የG+2 ግንባታ ከ4 ዓመት በላይ ስራው ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል :: በመሆኑም ከዚህ በፊት ግንባታውን ሲያከናውን ከነበረው አሸናፊ ድርጅት ውል ተቋርጦ በአዲስ መልክ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊው ድርጅት ተለይቶ ስራው እንዲጀምር ተደረጓል ። አሸናፊው ኮንትራክተር ለግንባታ ስራው የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል፣ ማሽነሪና የግንባታ ቁሳቁሶች በሚፈልገው መጠንና ጥራት አሟልቶ ስራ እንዲጀምር ከተቋሙ ጋር በውል ተፈራርሟል። አሸናፊው ድርጅት ከበደ ፈይሳ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የG+2 የምኝታ አገልግሎት ህንፃ ስራው ተጀምሮ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ከግንባታው ቦታ ርክክብ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ በ720 ቀናት ውስጥ አጠናቅቆ በውሉ መሠረት እንዲያስረክብ ተስማምቷል። ኮንትራክተሩ የG+2 የምኝታ ማደሪያ ህንፃ ለማስገንባት ያሸነፈበት ገንዘብ 45,590,473.50 / አርባ አምስት ሚሊየን አምስት መቶ ዘጠና ሽህ አራት መቶ ሰባ ሶስት ብር ከአምሳ ሳንቲም በሆነ ወጪ ግንታውን ሰርተው እንዲያጠናቅቁ ተደርጓል ።



