የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም የማኔጅሜንት አባላት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።

ተቋሙ በ2015 ዓ.ም በዕቅድ ተይዞ ሲከናወኑ የነበሩ ስራዎችን የተቋሙ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ገምግሟል።የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ተሰማ በሪፖርቱ ግምገማው ላይ እንዳሉት በዚህ ሩብ ዓመት እንዴት ስራችንን ስናከናውን እንደነበርና ዳይሬክቶሬቶች የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በጠንካራ ጎን የተሰሩ ስራዎች እንድናስቀጥል እንድሁም ታቅደው ባልተሰሩ ስራዎች ላይ በቀጣይ ሩብ ዓመት ተካተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የተቋሙ የዕ/በ/ዝ/ክ/ግ/ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን ሪፖርቱን እንድወያዩ አቅርበዋል።የማኔጅመንት አባላቱም በቀረበው ሪፖርት ላይ ታቅደው ባልተከናወኑና አፈፃፀሙ ዝቅተኛ በሆነበት ላይ ጥያቄና አስተያዬት በመስጠት የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *