የቦርድ አባላት የተቋሙን የብቃትና ምዘና የአቤቱታና ቅሬታ ዲሲፕሊን አፈጻጸም መመሪያ እና የተቋሙ የአገልግሎት ክፊያ መመሪያን መርምሮ አፀደቀ ።

(ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም አሶሳ )የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም የቦርድ አባላት የተቋሙን የብቃትና ምዘና የአቤቱታና ቅሬታ ዲሲፕሊን መመሪያና የተቋሙ የአገልግሎት ክፊያ መመሪያን መርምሮ አፅድቋል ///”///“”//***********************

የቦርዱን ውይይት መድረክ የመሩት የክልሉ ም/ርዕስ መስተዳድር ፣ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ እና የብቃትና ሥራ አመራር ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ለቦርድ አባላቱ ሰነዶች በዝርዝር እንዲቀርብና የቦርድ አባላቱ በሚቀርቡ መመረያዎችን ሀሳብና አስተያየት ሰጥተው እንዲያፀድቁ ጠይቀዋል።

በዚህ መሠረት ቦርዱ በመጀመሪያ ሰነዱ የተመለከተው የተቋሙ የብቃትና ምዘና አቤቱታና ቅሬታ ዲስፕሊን አፈጻጸም መመሪያን መርምሮ ማፅደቅ ሲሆን በዚሁም የቀረበውን መመሪያ በመገምገም የሚሻሻሉትን በማሻሻል መርምሮ አፅድቋል ።

ቦርዱ በሁለተኛነት ሰነድ የተመለከተው የተቋሙ የአገልግሎት ክፊያ መመሪያን መርምሮ ማፅደቅ ሲሆን ተቋሙ ከተሰጠው ኃላፊነትና ተግባር አንፃር ስልጠና በመሰጠትና በማስተባበር ፣በማማከር እንዲሁም ጥናትና ምርምር ስራዎች ሲያከናውን ለሰልጣኞች ለሚያቀርበው አገልግሎት ተመጣጣኝና ጊዜውን የዋጀ የአገልግሎት ክፊያ ማገኘት በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጀውን የአገልግሎት ክፊያ መመሪያ ለቦርድ በማቅረብ በተደረገው የዋጋ ማማሻያ መመሪያውን መርምሮ ማፅደቅ ሲሆን ቦርዱ በቀርቡ የአገልግሎት ክፊያ ዋጋ ዝርዝር ይዘቶችን በመመልከት ወቅታዊ የገበያ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ የተደረገውን የአገልግሎት ክፊያ ማሻሻያ መመሪያውን መርምሮ አፅድቋል ።

ሁለቱ ሰነዶች ለቦርድ አባላት በተቋሙ አማካሪ አቶ በላይ ለሙ እና የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሰፋዬ አቡኖ አማካኝነት ቀርቧል ።

ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *