እንኳን ወደ   የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥራ አመራር ተቋም በሰላም መጣችሁ!!የቤ/ጉ/ክ/መ/የሥራ አመራር ተቋም የሚሰጣችሁ አገልግሎቶች :

1.በየደረጃዉ የሚገኙ የክልል የመንግስት አካላት የሥራ አመራር ብቃት እንዲጎለብት አስፈላጊ
የሆኑትን፤የሥራ አመራር ስልጠናዎች፤ምርምሮችና የምክር አገልግሎቶች ፍላጎት ያጠናል፤

2.በጥናትና ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ለክልሉ ልማት ኃይሎች ከሥራ አመራር ጋር የተያያዙ የአጭርና
መካከለኛ ጊዜ ሥልጠናዎችን ይሰጣል፤

3.በተቋሙ የሚሰጡ የሥልጠና፣የምርምርና የምክር አገልግሎቶች ምን ያህል ተጨባጭ ለዉጥ
ሊያመጡ እንደቻሉ ለማወቅ የሚያስችል ጥናት በየጊዜዉ ያካሂዳል፤

4.በሀገሪቱ በተለይም በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት፣ስልጠና ጥናትና ምርምር ተቋማት ጋር
በመደጋገፍና በመቀናጀት ይሰራል፤

5.የስልጠናና የጥናት ፕሮጀክቶች በማዘጋጀት እንዲሁም የምክር አገልግሎቶችን በመስጠት ከተለያዩ
ምንጮች ገቢ የሚያገኝበትን ሁኔታ ይፈጥራል፤

6.ለሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች ተመጣጣኝ ክፍያ ሊያስከፍል ይችላል፣ዝርዝር አፈፃፀሙ በክልሉ
ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሚወሰን ሆኖ የሰበሰበዉን ገቢም ለስልጠና፣ለምርምርና ለምክር
አገልግሎቶች ማስፋፍያ ይጠቀማል፤

7.የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ዉል ይዋዋላል፣ይከሳል፣ይከሰሳል የሚሉ ስልጣንና ተግባራትን ይዞ የተቋቋም
ተቋም ነዉ፡፡

እንኳን ወደ   የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥራ አመራር ተቋም በሰላም መጣችሁ!!