(ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም ፣ አሶሳ )የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሁሴን ሀሰን በመንግሥት ሰራተኞች የፐርሶኔል መረጃ ቆጠራና ማረጋገጥ ሪፎርም ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ በተቋማችን ማዕከል ተገኝተው ከዑራ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ የተመራ የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ተጠሪ ባለሙያዎች ሉዑካን ጋር ውይይት አድረገዋል ////*
በውይይቱ መድረክ የክልሉ ቴክኒክ እና ሙያ የሱፐርቪዥን እስታቲክስ ባለሙያዎች ፣ የዑራ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና የሲቪል ሰርቪስ ጽ /ቤት ተጠሪ ባለሙያዎች እንዲሁም የተቋማችን ሰው ሀብት አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተገኝቷል።
የውይይቱን መድረክ የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሁሴን ሀሰን በማወያየት አስጀምረዋል ።
በውይይቱም በሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የመንግሥት ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ ቆጠራና ማረጋገጥ ሪፎርም ላይ እንዲሰሩ የተዋቀሩ ንዑሳን ኮሜቴዎችና የሱፐርቪዥን ባለሙያዎች የሥራ እንቅስቃሴ ያለበትን ሁኔታ በማንሳት በስፋትና በጥልቀት ተወይይቷል።
በመንግሥት ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ ቆጠራና ማረጋገጥ ሪፎርም ላይ እንዲሰሩ የተዋቀሩ የሲቪል ሰርቪስ ንዑሳን ኮሜቴዎችና የእስታቲክስ ባለሙዎች ሱፐርቪዥን እስካሁን በአሶሳ ዞን ወረዳዎች ተንቀሳቅሶ ያከናወኑት ስራዎች ፣ የገጠሙ ችግርች እንዲሁም የተወሰዱ መፍትሄዎችና ወደፊት በዘላቂነት ችግሩን ቀርፎ ለመስራት የታሰቡ አቅጣጫዎች ላይ መክረዋል ።
የሰራተኞች መረጃ ቆጠራና ማረጋገጥ ሪፎርም ላይ ተዋቅሮ እየሰሩ ያሉ ንዑሳን ኮሜቴዎችና የባለሙያዎች ሱፐርቪዥን በተቋማችን የሰራተኞችን መረጃ ቆጠራና ማረጋገጥ ሥራ እያከናወኑ ሲሆን የተቋማችን ሰራተኞች መረጃ ቆጠራና ማረጋገጥ ሥራ ያለበት አፈጻጸም ተገምግሞ ለሌሎች ልምድና ተሞክሮ የሚሆንበት ሁኔታ ላይ ግንዛቤ ተወስዷል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com




