የቤ/ጉ/ክ/መ ብቃትና ስራ አመራር ተቋም በመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በክብር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የተመራው ቡድን ከተቋሙ አመራር እና ከማናጀመንት አባላት ጋር በጋራ በመሆን ገምግሞዋል፡፡

(ነሐሴ 2/2018 ዓ.ም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ በክብር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የተመራው ልዑካን ቡድን ከተቋሙ አመራር እና ከማኔጅመንት አባላት ጋር በጋራ በመሆን በመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ እየተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን ገምግሞዋል*//////**///

ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ክብር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ያሉ በመንግሥት አገልግሎትና አሰተዳደር ሪፎርም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን ከተቋሙ አመራሮችና ማናጀመኔት አባላት ጋር በመሆን የአፈፃፅም ሂደቱን የገመገሙ ሲሆን በዚሁም በመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፆ በቀጣይ ቀሪ ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ መሥራት እንደሚጠበቅ በአፅንኦት ገልጸዋል ፡፡

ከዚህ በተጨማርም በተቋሙ እየተገነባ ያለው የሰልጣኞች ማደሪያ ዶርምተሪ ህንፃ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ከግንባታው ኮንተራክተሮች አማካኝነት ተዟዙረው ጎብኝቷል ።

በጉብኝቱ ወቅት የግንባታው ኮንተራክተሮች የግንባታው ሂደት ያለበትን ሁኔታ ለርዕሰ መስተዳደሩ ገለፃ አድረገዋል ። ከህንፃው ጉብኝት ማጠቃለያ በኃላ በተቋሙ እየለሙ ያሉ የተለያዩ የሌማት ትሩፋቶችን ጎብኝቷል።
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *