በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ አጀሊ ሙሣ የተመራ የተቋሙ ሰራተኞች ሉውካን በአሶሳ ዞን ዑራ ወረዳ ሰልጋ 22 ቀበሌ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ላይ በመሣተፍ የአረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጧል //////////***/*
(ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ፣ አሶሳ )የቤ/ጉ/ክ/መ/ሥራ አመራር ተቋም ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ አጀሊ ሙሣ የተመራ የተቋሙ ሰራተኞች ሉዑካን ከሌሎች ሴ/መ/ቤቶች ጋር በመሆን የክልሉ መንግሥት ባስቀመጠው ስምሪት መሠረት በአሶሳ ዞን ዑራ ወረዳ ሰልጋ 22 ቀበሌ ተገኝተው “በጋራ ተስፋችን እንትከል “በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ቦታ ላይ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም አድረገዋል ።
በዘንድሮው ዓመት እንደ ሀገር በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተደረገው ሀገራዊ ጥሪ መሰረት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንድ ጀምበር 15 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዘው ቅደመ ዝግጅት ሥራዎች የተጠናቀቁ ሲሆን በሀገር ደረጃ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ ክፍል የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል ።
ይህን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ ፕሮግራም ጥሪን ከግብ ለማድረስ በክልሉ መንግሥት በተዋቀረውና በተሰጠው ስምሪት መሰረት የተቋማችን ሰራተኞች ሉዑካን ከሌሎች ሴ/መ/ቤቶች ጋር በጋራ በመሆን በአሶሳ ዞን ዑራ ወረዳ ሰልጋ 22 ቀበሌ ተገኝተው በተዘጋጀው ቦታ ላይ በንቃት በመሣተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጧል ።
በችግኝ ተከላው መርሀ ግብር ላይ የተገኙ ሰራተኞች ባስተላለፉት መልዕክት መንግሥት በየ ዓመቱ ለአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ዕቅድና የሚሰጠው ንቁ ተሳትፎ ለሀገሪቱ ደን ሽፋን ትልቅ አስተዋጽኦ ከማበርከቱ በተጨማሪ ለኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሚውሉ ችግኞች በስፋት መተከላቸው ትልቅ ቦታ የሚሰጥ መሆኑን በመግለፅ ይህም የሚደገፍና የሚበረታታ እንዲሁም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ እንደሆነና በዘመቻ የሚተከለውን ያህል የተተከሉትን ችግኞች ተንከባክቦና ጠብቆ ለታለመለት ዓላማ የማዋል ችግር የሚታይበት በመሆኑ መንግስት ልዩ ትኩረት በመሥጠት ሁሉም ዜጋ በኃላፊነትና በትጋት ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርግ መሰራት እንዳለበት ሀሳባቸውን ጨምሮ ገልጿል
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com












