አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም የኮምፒውተርና የኢንተርኔት መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

አሶሳ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም — የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በጥናትና ምርምር፣ በስልጠናና በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማቴሪያል ድጋፍ ዘርፎች የጋራ ትብብር ለማድረግ በገቡት ስምምነት መሠረት ዩኒቨርሲቲው ለተቋሙ የኮምፒውተር ድጋፍና የተለያዩ የኢንተርኔት መሳሪያዎችን አበረከተ*///////*

ድጋፉ ዛሬ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ አማካኝነት ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም ተላልፏል።

የብቃትና ሥራ አመራር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አጀሊ ሙሳ በድጋፉ አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ተቋሙ ያገኘውን ድጋፍ በተለይም የኮምፒውተር ላብራቶሪውን ለማጠናከርና የስልጠና አቅሙን ለማሳደግ እንደሚያውለው ገልጸዋል።
አቶ አጀሊ ሙሳ አክለውም፣ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተቋሙ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሁለቱ ተቋማት የትብብር ስምምነት በተግባር እየተተረጎመ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ጠቁመው፣ ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ዕውቅናና ምስጋና አቅርበዋል።

የተደረገው ድጋፍ የተቋሙን የዲጂታል መሠረተ ልማት በማጠናከር፣ የኮምፒውተር ላብራቶሪውን በማሻሻል እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስልጠና አገልግሎትን በማስፋፋት ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በቀጣይም ሁለቱ ተቋማት በጥናትና ምርምር፣ በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በሌሎች የትብብር መስኮች ያላቸውን ትስስር በማጠናከር ለክልሉ የሰው ኃይል ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ የበለጠ አስተዋጽኦ ለማድረግ እንደሚሰሩ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *