ለተቋሙ ማኔጅመንት አባላትና አማካሪዎች እስትራቴጂክ የዕቅድ አስተቃቀድ ስነ ዜዴ(KPI)key performance Indicators ሂደት ዙሪያ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየወሰዱ ነው

(ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፣ አሶሳ )የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም ማኔጅመንት አባላትና አማካሪዎች እስትራቴጂክ የዕቅድ አስተቃቀድ ስነዜዴ(KPI)በ ሂደት ዙሪያ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል /////////

በስልጠናው መድረክ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ሥዩም ተገኝተው ስለ ሥልጠናው ዓላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላትና አማካሪዎች ገለፃ በማድረግ ስልጠናው ለተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ገልፆ በስልጠናው ላይ በንቃት በመሳተፍ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ በአፅንኦት ተናግሯል ።
ስልጠናው ከቀን 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው እየተሰጠ ያለው ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡት ሲነረ አማካሪ በአቶ አብዱለሀለዕቅ ረሽድ አማካኝነት ነው ።

ስልጠናው “ተግባራዊ የስራ አፈጻጸም አመራር እና እውነተኛ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች” ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ትርጉም ላላቸው እና በትክክለኛ ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉ ነገሮች ላይ ትኩረት መስጠትን በማሳየት የለውጥ ፍሬዎችን ለመለካት እሰከመጨረሻው ድረስ የሚያስኬድ ተጨባጭ ውጤት የሚፈልግ የሥራ አፈጻጸምና አመራር ሂደት ሲሆን ይህ በንድፈ-ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ስራ ላይ ሊተገበር የሚችል የስራ ግምገማን ይገልጻል ።

እነዚህ True( KPIs) key performance indicators ተራ መረጃዎችን ሳይሆን የተቋሙን ወይም የባለሙያውን ስኬት በትክክል የሚያሳዩ መለኪያዎችን የሚመለከት እውነተኛ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካችም ነው ።

ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *