(ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም ) የቤ/ጉ/ክ/መ/ ብቃትና ሥራ አመራር ተቋም ሠራተኞች በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ በተዘጋጁ የሪፎርም ሰነዶች ላይ ከነሐሴ 13 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል*/////**/////*
የውይይቱን መድረክ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ አጄሊ ሙሳ ከመላው ሰራተኞች ጋር በመሆን ያስጀመሩ ሲሆን የውይይቱም ዓላማ በተቋሙ የሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ የተዘጋጁትን ሰነዶች በሠራተኞች ደረጃ በማየት፣ ግብዓትና አስተያየት በማሰባሰብ ሰነዶቹን የበለጠ ግልጽ፣ ተግባራዊና ተቋማዊ አቅምን ያገናዘበ ለማድረግ መሆኑን ተገልጿል።
ሰነዶቹ የተዘጋጁት ተቋሙ ባደራጃቸው ልዩ ልዩ ንዑስ ኮሚቴዎች ሲሆን፣ በኮሚቴዎቹ የተዘጋጁት ሰነዶች በተቋሙ ማኔጅመንት በዝርዝር ከተገመገሙ በኋላ ለሠራተኞች ቀርበዋል።
በዚህም ሠራተኞች በሰነዶቹ ይዘትና አተገባበር ዙሪያ ሀሳቦችን በማንሳት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ከቀረቡት የሪፎርም ሰነዶች መካከል ፦
✔የብዝሃነትና አካታችነት
✔የሠራተኞች የሰው ኃይል ስምሪት
✔የተለያዩ የተቋሙ የአገልግሎት ክፍያ መመሪያዎችን በተቋማዊ አሠራር ፍትሾ ማስተዳደር እንዲሁም
✔በሰራተኞች ብቃት ማዕቀፍ መመሪያ በሚሉ ሰነዶች ላይ ያተኮረ ውይይት ነበር :
በተለይም በሰነዶቹ ላይ የቀረቡ ግብዓቶች የሪፎርም ስራዎችን ከተቋሙ ዕለታዊ አሠራርና ከሚጠበቀው የተቋም ለውጥ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ ጠቃሚ መሆናቸው ተጠቁሟል ።
የተቋሙ ሠራተኞች በውይይቱ ላይ በንቃት በመሳተፍ በሰነዶቹ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን፣ አስተያየቶችንና የማሻሻያ ሀሳቦችን አቅርበዋል። የተሰጡት ግብዓቶችም በቀጣይ የሰነዶቹ ማሻሻያና የመጨረሻ ማጽደቅ ሂደት ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቋል።
ይህ የውይይት መድረክ በተቋሙ የሪፎርም ሥራዎች ላይ የሠራተኞችን ተሳትፎ በማሳደግ፣ ተቋማዊ የጋራ ግንዛቤን በማጎልበት እና በተግባር የሚውሉ የሪፎርም ሰነዶችን ለማዘጋጀት ጠቃሚ መሠረት እንደሚጥል ይታመናል ።
በመንግሥት አገልግሎትና አሰተዳደር ሪፎርም ሥራ ጋር ተናብበውና ተቀናጅተው የቀረቡ ተከታታይ ሰነዶች ላይ የተቋሙ ሰራተኞች ሰፊ ውይይትና ሀሳብ በማንፀባረቅ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ለሪፎርም ስራው ዝግጁ መሆናቸውን በመድረኩ ገልጿል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com




























