በፓዊ ወረዳ ከአንድ መቶ አንድ ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የማዕድ ማጋራት እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
( ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ )የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ብቃትና ስራ አመራር ተቋም በመተከል ዞን በፓዊ ወረዳ መጪውን አዲስ ዓመት እና ጳጉሜ 5 የነገው ቀንን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች እና ለተማሪዎች የመደጋገፍና የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል*///**//////
በዚሁ መርሃ ግብር ለ20 አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት እንዲሁም ለ50 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከአንድ መቶ አንድ ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ለተጠቃሚዎች ማዳረስ ተችሏል።
የፓዊ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ አሰፋ፤ ተቋሙ ላደረገው በጎ አድራጎትና ተግባር ምስጋና አቅርበው፥ በዓላትን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን ማስታወስና ማገዝ የባህላችንና የደስታችን አካል ማድረግ ይገባል ብለዋል።
መሰል ድጋፎች የማህበረሰቡን የመደጋገፍ እሴት የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብቃትና ስራ አመራር ተቋም የግዥ ባለሙያ አቶ አብዱ ሙዬ ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በዓሉን ምክንያት በማድረግ የማህበረሰቡን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች ለመደገፍና ደስታቸውን ለማካፈል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
አቶ አብዱ አክለውም፣ አዲሱን ዓመት ስናከብር አቅም የሌላቸው ወገኖቻችንን በማሰብና ከጎናቸው በመቆም መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፥ ይህ ድጋፍም የወገን አለኝታነትን ለማሳየትና ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ በማሟላት ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑት አቅመ ደካሞች እና የተማሪ ወላጆች በሰጡት አስተያየት፤ በበዓል ዋዜማ በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ መደሰታቸውን ገልፀው፥ ድጋፉ ለአዲስ ዓመት በዓል ዝግጅታቸው ትልቅ እፎይታን የፈጠረላቸው መሆኑንና ለልጆቻቸው የተሰጠው የትምህርት ቁሳቁስም የትምህርት ዘመኑን ያለስጋት እንዲጀምሩ የሚያስችላቸው መሆኑን በመጥቀስ ድጋፍ ላደረጉላቸው ተቋሙ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የክልሉ ብቃትና ስራ አመራር ተቋም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለው ቁርጠኝነት በፓዊ ከተማ 02 ቀበሌ ለሚገኙ አንድ አቅመ ደካማ የሚሆን የመኖሪያ ቤት ግንባታ እያከናወነ ይገኛል።
መረጃው: ከመተከል ዞን ፓዊ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ድረ -ገፅ ላይ የተወሰደ ነው ።









