የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሥራ አመራር ተቋም የ2016 በጀት ዓመት የተጠቃለለ ሪፖርት በተቋሙ ማኔጅመንት አባላት ግምገማ ተደረገ ።

ሥራ አመራር ተቋም ( ሰኔ 19/2016 ዓ.ም. ፣ አሶሳ ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሥራ አመራር ተቋም የ2016 በጀት ዓመት 12 ወራት የተጠቃለለ ሪፖርት በተቋሙ ማኔጅመንት አባላት ግምገማ ተደርጓል ።*/*/*/*/*/*/***/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/

የበጀት ዓመቱን ሪፖርት ለተቋሙ ማኔጅመንት አባላት ያቀረቡት የተቋሙ ዕቅድና ዝግጅት ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን ሲሆኑ በቀረበው  የተጠቃለለ ሪፖርት ላይ ሁሉም ማኔጅመንት አባላት ተገኝተው የአፈፃፀም ደረጃውን በጥልቀት ገምግሟል ።

በግምገማ ወቅት በጥቅል ሪፖርቱ የቀረቡ ጠንካራ ጎኖች በበጀት ዓመቱ በክልሉ የተለዩ ሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ዙሪያ የተሰሩ የለውጥ ሥራዎች ውስጥ አንዱ በካይዘን ትግበራ አፈጻጸም ከፍተኛ ወጤት የታየበት መሆኑን በማኔጅመንት አባላት የተገመገመ ሲሆን በተጨማሪም በተቋሙ እየተገነቡ ያሉ የማስፋፊያ ግንባታዎች አፈጻጸም የተሻለ እንደሆነ እና የቁጥጥርና ክትትል ሥራዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

በመጨረሻም እንደ ተቋም ከአቻና አጋር ተቋማት ጋር የሚደረገው የጋራ ትብብርና ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ማድረግ የሚሉና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ግምገማው ተጠናቋል ::

ለተጨማሪ መረጃዎች:-
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Email Address
info@bgrsmi.gov.et
Telegram Address
https://t.me/bgrsmi
Twitter address :-@Benishangu45217

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *