(ነሐሴ 09/2016 ዓ.ም. አሶሳ ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሥራ አመራር ተቋም ቦርድ አባላት የ2016 የተጠቃለለ ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ገመገሙ */*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*
ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት በዕቅድ ይዞ ሲያከናውናቸው የነበሩ ስራዎችን አፈጻጸም ሁሉም የቦርድ አባላት በተገኙበት ገምግሟል ።
የተቋሙ ቦርድ ሰብሳቢ ፣ የክልሉ ም/ ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቨስ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳና ሁሉም ቦርድ አባላት በተገኘበት የ2016 በጀት ዓመት የተጠቃለለ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደረጓል ።
የተቋሙን በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ለቦርድ አባላት በሰነድ ያቀረቡት የተቋሙ እቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን ሲሆኑ በቀረበው ዝርዝር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የበቀጣይ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ቦርድ አባላት በሰፊውና በጥልቀት ግምገማና ውይይት ያደረጉ ሲሆን ተቋሙ ከተሰጠው ስልጣንና ተግባራት አኳያ ያከናወናቸው ሥራዎች እጀግ ውጤታማና አበረታች መሆናቸውን በግምገማ ወቅት የተነሱ ሲሆን ተቋሙ ከተሰጠው ኃላፊነት እና ተግባር ጎን ለጎን በተቋሙ ቅጥር ግቢ ያከናወናቸው የልማት ትሩፋቶች እንዲሁም የማስፋፊያ ግንባታ ስራዎች መፋጠንና ያሉበት ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን በግምገማ ወቅት በሰፊዉ ተነስቷል ።
ሌላው በአፈፃፅም ወቅት በአንዳንድ ስራዎች ላይ ለታየው ውስንነት ማነቆ የነበረው የበጀት እጥረት መሆኑ ተገልጾ በቀጣይ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በተሸለ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ቦርዱ የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች:-
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Email Address
info@bgrsmi.gov.et
Telegram Address
https://t.me/bgrsmi
Twitter address :-@Benishangu45217








