(አሶሳ፣ ሚያዝያ 12/2016 ዓ.ም) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሥራ አመራር ተቋም የ2016 በጀት አመት 3ኛ ሩብ አመት የ9 ወራት ጥቅል ሪፖርት ከተቋሙ የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ገምግሟል።
ጥቅል ሪፖርቱ በተቋሙ ዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ሀይማኖት ሙሉቀን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ውይይቱን የመሩት የክልሉ ም/ ርዕሰ መስተዳደር እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የተቋሙ ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጌታሁን አብዲሳ የ2016 በጀት አመት 3ኛ ሩብ ዓመት የ9 ወራት አቅድ አፈፃፀም ጥቅል ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በዋነት በካይዘን የተሰሩ ስራዎች አበረታች በመሆናቸው ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ የምርምር ስራዎችና የማማከር አገልግሎት ትኩረት ተሰጥተው መሰራት እንዳለባቸው እንዲሁም በቀጣይ ተቋሙን ወደ አካዳሚ ለማሳደግ ተቋማዊ አቅም መታየት እንዳለበት በግምገማው ተመላክቷል።
እንደ አጠቃላይ የተቋሙ 9ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ውጤታማ ሥራዎች የተከናወኑበት ሲሆን በሪፖርቱ የተመላከቱ ጉድለቶችን ለመቅረፍ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በውይይቱ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል ውስንነቶችን ደግሞ ለማስተካከል በሚቻልበት ሁኔታ የጋራ ተደርጓል።
በተጨማሪም የቦርድ አባላት በተቋሙ እየተገነቡ ያሉ የሰልጣኞች G+2 ማደሪያ ህንፃ እና መሰብሰቢያ አዳራሽ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ለተጨማሪ መረጃዎች:-
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Email Address
info@bgrsmi.gov.et
Telegram Address:- https://t.me/bgrsmi
Twitter :- @Benishangu45217




