የክልሉ መንግስት መስተዳደር ም/ቤት በወሰነው ውሳኔ መሰረት ቀደም ሲል ተቆፍሮ የነበረውን የጥልቅ ውኃ ጉድጓድ የዝርጋታና ቀሪ ስራውን ለጉሌ ውኃና ኮንስትራክሽን ድርጅት በቀጥታ እንዲሰጥ እና ስራው እንዲሰራ በተወሰነው መሰረት ተቋሙ ከድርጅቱ ጋር በዛሬው ዕለት የሳይት ርክክብ /Site hand Over / አድርጓል።
የርክክብ ስራውም በተቋሙ እያጋጠመ ያለውን የውኃ አቅርቦት ችግር እና በአዲስ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የሰልጣኞች ማደሪያ ዶርሚተሪና መሰብሰቢያ አዳራሽ በቂ የሆነ የውኃ አቅርቦት እንዲኖረው በማሰብ መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር በርክክቡ ወቅት የገለጹ ሲሆን ስራው በተቻለ መጠን በቅርቡ ተጀምሮ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ አሳስበዋል ።
በርክክቡ ወቅትም ከክልሉ ውሃና ኢነርጂ ልማት ቢሮ አቶ አብዱረሂም አልፈኪ እንዲሁም ከጉሌ ውኃና ኮንስትራክሽን ድርጅት ወ/ሮ ትቅደም ሞርካ የተገኙት ሲሆን ስራውን ከዛሬ ጀምሮ ትኩረት ሰጥተን በተያዘለት ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ስራውን ለማስረክብ የበኩላቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።
ለተጨማሪ መረጃዎች:-
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Email Address
info@bgrsmi.gov.et
Telegram Address:- https://t.me/bgrsmi
Twitter :- @Benishangu45217

