ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ፣ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም )
የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም በተቋሙ እየተገነቡ ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ በክልሉ ም/ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጉብኝት ተደረገ ።
በተቋሙ በ2014 ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ የቆየውና በ2014 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው G+2 የሰልጣኞች ማደሪያ ህንፃ አሁን ያለበት የስራ አፈጻጸም ደረጃ በቋሚ ኮሚቴ አባላት ጉብኝት የተደረገ ሲሆን አጠቃላይ የተቋሙ እንቅስቃሴና የግንባታዎች አፈፃፀም ደረጃ በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ዩሐንስ ተሰማ ገለፃ ተደርጓል ።
አቶ ዩሐንስ እንደገለጹት እየተገነቡ ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲጠነቀቁና ይህንንም ስራ ለማፋጠን የበጀት/የፋይናንስ ችግር እንዳለ ለቋሚ ኮሜቴ አባላት ገለጻ አድርገዋል ።
በተጨማሪም ግንባታዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁና እንዲፋጠኑ የተያዘላቸው በጀት በወቅቱ ተለቆ ስራው እንዲሰራና እንዲጠናቀቅ ለቋሚ ኮሚቴዎች ያሳሰቡ ሲሆን ዋናው ትልቁ እንቅፋትም ኮንትራክተሮች ስራውን እንዳያፋጠኑ የሚያደርጋቸው ምክንያት የክፊያ መዘግየትና የበጀት እጥረት እነደሆነ ተገልጿል ።
ኮንትራክተሮች በሰጡት ቃለ መጠይቅ ለግንባታው መጓተት ዋና ችግሩ ለስራ ማስኬጂያ የሚሆን የክፍያ መዘግየት ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የግንባታ ግብዓቶች የዋጋ ንረትና ግብዓቶች በወቅቱ እንዳይደርሱ በመንገድ ላይ የፀጥታ ችግርና የትራንስፖርት ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ከላይ የተገለፁ ችግሮች ከተቀረፉ ስራው በተያዘለት ጊዜ በ2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ገልጸው አሁን ግንባታዎች ያሉበት ደረጃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 55% ከመቶና G+2 የሰልጣኞች ማደሪያ ህንፃደግሞ 53% ከመቶ መድረሱን ለቋሚ ኮሜቴዎች ገልፀዋል ።
የክልሉ ም/ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሜቴ አባላት በጉብኝቱ ወቅት የተመለከቱትንና የተደረገላቸውን አጠቃላይ ገለፃ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት አድርገው የመፍትሄ አቅጣጫ እንደሚሰጥበት ገልጸው በተያዘው ክረምት በተቋሙ እየለማና ለአገልገሎት እየዋለ ያለውን የአትክልት ምርቶች ተዘዋውረው ተመልክቷል ።
