የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በተቋሙ ማኔጀመንት አባላት በተዋቀረ ኮሜቴ ዝርዝር ዕቅድ ቀርቦ ከተቋሙ ኃላፊና አማካሪዎች  ጋር ውይይት ተደረገ ።

ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ፣ ሐምሌ 26/2015 ዓ.ም )
የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በተቋሙ ማኔጅመንት አባላት በተዋቀረ ኮሚቴ የተቋሙ አመታዊ ዕቅድ ዝርዝር ሁሉም ማኔጅመንት አባላትና የተቋሙ ኃላፊውና አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደረገ */*/*/*/*/*

ተቋሙ በ2016 በጀት ዓመት የዓመቱን ዝርዝር ዕቅድ ከክልሉ ፕላን ኮሚሽን በተሰጠ አቅጣጫ መሠረት አዘጋጅቶ በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር በተዋቀረ ማኔጅመንት ኮሚቴ ቀርቦ ለሁሉም ማኔጅመንት አባላትንና ለተቋሙ አማካሪዎች ዝርዝር ዕቅዱ የቀረበ ሲሆን በተዘጋጀው ዕቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በውይይቱ ወቅት የዓመቱ ዝርዝር ዕቅድ ከበፊቱ ዕቅድ አዘገጃጀት አንፃር በዘንድሮው ዓመት ለአሰራር ግልጽና አመቺ በሆነ መልኩ መቅረቡ ለዕቅዱ መሳካት ውጤታማ እንደሚሆን በተቋሙ አማካሪዎች አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በተቀመጠው ዝርዝር ዕቅድ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያና እንደ ተቋም በዝርዝር ዕቅድ ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች ተካተዉ ለአሰራር በሚመች መንገድ የተደረገ ሲሆን  በተለይ በተቋሙ ውጤት ተኮር ስራዎች ላይ በትኩረት መሠራት እንዳለበት  በአማካሪዎች አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ  በጥልቀት  ከተወያዩ በኃላ አጠቃላይ የዓመቱ ዕቅድ ወደ ስራ ለማስገባት በተቋሙ የበላይ አመራርና በቦርድ አባላት እንደሚፀድቅ  አቅጣጫ ተቀምጧል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *