የስራ አመራር ተቋም ማኔጅመንት አባላት በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጀት ዙሪያ ውይይት  አደረገ ።

ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ፣ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም )
የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ ተቋም ማኔጅመንት አባላት በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅትና አተገባበር  ዙሪያ ውይይት አካሄዱ */*/*/*/*/*

በዚህ ውይይትም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ማሳደግ ላይ በቀጥታ ኢላማ ያደረጉ ተግባራት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ በተቋሙ የበላይ አመራር የተዋቀረው የዕቅድ ዝግጅት ኮሜቴና የማኔጅመንት አባላት አቅጣጫ አስቀምጧል ።
እቅዱ ዋና ዋና  የትኩረት መስኮቶችንና አቅጣጫዎችን የያዘ ሲሆን የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምን መሠረት አድርጎ እየተዘጋጀ መሆኑን የተቋሙ ዕቅድና ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳ/ር አቶ ሐይማኖት ሙሉቀን ገልጸዋል ።
የክልሉ ፕላን ኮሚሽን አቅጣጫ በሰጠው መሠረት የተዘጋጀው ዕቅድ በውጤት ተኮር አግባብ የተቃኘ ሲሆን ተጠያቂነትንም የሚያሰፍን መሆኑንና በቀጣይ ከስራ ክፍሎች ጋር በመፈራረም ስራዎችን ቆጥረው ይቀበላሉ ሲሉ የተቋሙ የበላይ አመራር ገልጸዋል ።

በተጨማሪም ሁሉም የስራ ክፍሎች ያቀዱትን ዕቅድ በዝርዝር ማወቅ ይኖርባቸዋል ለዚህም የየክፍሉ የስራ ኃላፊዎች ለእያንዳንዱ ተግባር ከሠራተኞች ጋር በግልጽ መነጋገርና የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባና እቅዱ የባለቤትነት ስሜት  በሰራተኛው  ዘንድ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባ በተቋሙ የበላይ አመራር አቅጣጫ ተቀምጧል ።

በዚህም እቅድ ዙሪያ በተቋሙ ዕቅድና ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳ/ር  እንደገለፁት ዕቅድ ለአንድ ተቋም ራዕይና ተልዕኮን ለማሳካት አይነተኛ መሳሪያ መሆኑን ጭምር ገልጸዋል ። በዚህ ዕቅድ ዝግጅት ስራ ላይ ሁሉም የተቋሙ የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች በተቋሙ የአንድ ዓመት ዕቅድ ላይ ጥልቅ ውይይትና የስራ መግባባት የተፈጠር  ሲሆን በቀጣይም የተዘጋጀ ያለውን ዕቅድ በተቋሙ አማካሪዎችና ተመራማሪዎች አማካኝነት አስተያየት ተሰጥቶበት በበላይ አመራሮች ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *