ተቋሙ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ይዞ ሲተገብራቸው የነበረው የስራ አፈፃፀም ምን ይመስላል በሚለው ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ የተደረገ ሲሆን ሪፖርቱን የስራ አመራር ተቋም የዕቅድና ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን አቅርበዋል።
የስራ አመራር ተቋም ቦርድ ሰብሳቢና የክልሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መሐመድ አብዱላዚዝና ሁሉም የቦርድ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም ደረጃ ገምግመዋል ።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ በ2015 ዓ.ም በ4ኛ ሩብ ዓመት (በ12 ወራት ) ታቅዶ በከፍተኛ ውጤት የተከናወኑ ፣ ውስንነት የታዩባቸው ፣ በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጥልቀት በመወያየት ጥያቄና አስተያየት የተደረገ ሲሆን እንዲሁም በተቋሙ ግብዣ እና አዘጋጅነት በሚደረጉ የምርምር ኮንፍረንስ ፣ አውደ ጥናት ፣ወርክሾፕ እና ሴሚናር የምርምር ውጤት ለሚያቀርቡ አካላት የሚከፈል ክፍያንና በተቋሙ እየተገነቡ ያሉ የማስፋፊያ ግንባታዎች ያሉበት ደረጃ መገምገምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ዙሪያ ተወያይቶ ወሳኔ በማፅደቅ ተጠናቋል ።



