የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም ሠራተኞች ለጀግናው ሀገር መከላከያሠራዊት የደረቅ ስንቅ ድጋፍ አደረጉ!

እንደሚታወቀዉ አሸባሪው ህወሃት ከስልጣን ከተወገደ ቀን ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል በመኮብለል መቀሌ ውስጥ በመመሸግ እኔ ካልገዛሁ ኢትዮጵያ ትፈረሳለች በሚል የተሳሳተ አመለካከት ይዞ የገዛ እናት ሀገሩን ለመውጋት የጦርነት ሰነድ በመሰነድ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጦርነት መክፈቱ ይታወቃል ።ይህ የሽብር ቡድን አላማው የሰሜኑን የሀገር መከላከያ ሠራዊት እዝ በማጥቃት በሀይል ወደ ስልጣን የመምጣት ህልም ነበረው *******ይህ ቡድን የሀገር ዋልታና መከታ የሆነውን ጀግናዉ የሀገር መከላከያሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በመክፈት ጦርነት በይፋ መጀመሩ ግልጽ ነው።ይህን የሽብር ቡድኑን ድርጊት የተመለከተው ሀገር ወዳዱው መላው የኢ/ያ ህዝብ በአራቱ አቅጣጫ እንዴ ንብ ሆ ብሎ በመነሳት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሆን ከመሸገው ምሽግ ከትግራይ ክልል ህዝብ ቡድኑን ነጥሎበመምታት ህግ የማስከበር ስራ መሰራቱ ይታወቃል ***************

ነገር ግን መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ የሠላም ዋጋን በመረዳት ቅድሚያ ለሠላም ብሎ የሠላምአማራጮችን ቢያመቻችምየሽብር ቡድኑ አሻፈረኝ በማለት 1ኛ ፣2ኛና 3ኛ ዙር እያለ የጦርነት እስትራቴጂሠነድ በማዘጋጀት ሀገርን እና ህዝብን የማዋረድ አላማ አንግቦ እንዲሁም የብልፅግና ጉዞን ወደ ኋላ ለመመለስ በአሁኑ ሰዓት 3ኛ ዙር ጦርነት መክፈቱይታወቃል ***************/////////*****************************

የሽብር ቡድኑ የከፈተውን ጦርነት መላው የኢ/ያ ህዝብ ለመመከትና ለማስወገድለሠራዊቱ ደጀን በመሆን በግምባርና የተለያዩ የሎጂስቲክ አቀርቦቶችን በማድርግ ላይ ይገኛል **** በመሆኑም ቤ/ጉ/ክ/መ/ እንደ ክልልም ብሎ እንደ ሀገር የመጣውን ጦርነት ለመመከት የተለያዩ ድጋፎችን በማድርግ ላይ ይገኛል***በዚህ መሠረት የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም ሠራተኞች ለጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት መንግስት ባቀረው ጥሪ መሠርት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተቋሙ ሴት የመንግስት ሰራተኞች የደረቅ ስንቅ ዝግጅት በማድረግ ድጋፋቸውን አሳይተዋል /////*********////////////

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *