ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ፣ ግንቦት 25/2015)ዓ.ም. የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም ሠራተኞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ፕሮግራም አካሄዱ */*/*/*/*/*/*/*//*
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠቃለያ ምዕራፍ ዙሪያ ከክልል ከመጡ የሴቶች አደረጃጀት ሊግ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር የቦንድ ሽያጭ ፕሮግራም ተካሄዷል ።
የስራ አመራር ተቋም ሠራተኞች ከክልል ከመጡ የሴቶች አደረጃጀት ሊግ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር ስለ ኢ/ያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበት ደረጃ ላይ በሰፊው ከተወያዩ በኋላ ግድቡ አሁን ላይ ያለበት የግንባታ ደረጃ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ በመድረሱን እና 4ኛ ዙር የውሃ ሙሊት ለማድረግ በጉጉት እየተጠባበቀ በመሆኑ እንደ ከዚህ በፊት ሁሉ የተለመደውን የቦንድ ሽያጭ በማድረግ የኢ/ያ ህዝብ የመጨረሻ አሻራውን በማሳረፍ ግንባታውን በስኬት ለማጠናቀቅ በመላው ኢ/ያ የቦንብ ሽያጭ ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ የሴቶች አደረጃጀት ሊግ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለተቋሙ ሰራተኞች ማብራሪያ ሰጧል።
የተቋሙ ሰራተኞች ስለ ታላቁ ኢ/ያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አስፈላጊነትና ግድቡን ከጫፍ ለማድረስ እያንዳንዱ ዜጋ ሀላፊነት እና ግዴታ በመሆኑ የራሱን አሻራ ከማሳረፍ ወደኋላ እንደማይል በሰፊው ከተወያየ በኋላ እስካሁን ግድቡ ከተጀመረ ቀን ጀምሮ 8100 ላይ A ቁጥር በመላክ ከአንድ ብር ጀምሮ የተጀመረው ድጋፍ ከፍ ብሎ ከ500-1000 ብር የቦንድ ሽያጭ በማከናወን ላይ መሆናቸውን በማስረዳት የተለመደውን ድጋፍ በማድረግ ግድቡን በስኬት እንደሚያጠናቅቁ በመተማመን በዘንድሮው 2015 ዓ.ም. ከ200-2000 ብር ቦንድ ሽያጭ ለማድረግ ከወር ደሞዛቸው ገቢ እንደሚያደርጉ ቃል ገብቷል ።
@@@ መረጃው ከስራ አመራር ተቋም የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳ/ር ነው ::
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com




