ስራ አመራር ተቋም በቅርቡ ያስጀመረው የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቀቀ ።

ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ፣ሚያዚያ 25/2015)ዓ.ም የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም የተቋሙን የውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በኡራ ወረዳ በባሮ ቀበሌ ያስጀመረው የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ */*/*/*/*/*

የተቋሙን የውሃ ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ከBG development group Construction ቢሮ ጋር በመተባበር የተጀመረው የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በስኬት በመጠናቀቁ በቀጣይ በታቀደለት ጊዜ አቅርቦቱን ወደ ተቋሙ ለማዳረስ የመስመር ዝርጋታ እንደሚቀር የተገለፀ ሲሆን ዝርጋታው መጠናቀቅ የተቋሙን የውሃ ችግር በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚቀርፍ ተገልጿል ።

የተቋሙን የውሃ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በታቀደለት ጊዜ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በስኬት እንዲጠናቀቅ የBG development group Construction ቢሮ ላደረገው  አስተዋጽኦ ተቋሙ አመሰግኖ በቀጣይ ቀሪ ስራዎች እስኪጠናቀቁ ድረስ ድጋፉን አጠናክረው እንዲቀጥል አሳስበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *