ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ) የካቲት 29/2015 ዓ.ም
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ስራ አመራር ተቋም ከክልል ሴ/መ/ቤት ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ ።
የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ ተቋም ከክልል ሴ/መ/ቤቶች ከሚገኙ ከተመረጡ ተቋማት ጋር የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ እና የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ መመሪያ ዙሪያ የተዘጋጀ የግንዛቤ መሰጫ እና የምክክር መድረክ አካሄደ ።
የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ምትኬ ሮቤ ከክልል ሴ/መ/ቤት ባለድርሻ አካላት እና የመድረኩ ታዳሚ እንዲሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ እና የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ መሸጫ መድረክ አቀረቡ ።
አቶ ምትኬ ሮቤ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ እና የተሻሻለውን የክፍያ መመሪያ ዙሪያ የተዘጋጀ የግንዛቤ መሸጫ መድረክ ላይ ለባለድርሻ አካላት በሰጡት መግለጫ ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ እና ሃላፊነት መወጣት ከሚችሉባቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ውስጣዊ አቅምን ማጠናከርና ከሌሎች ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ሲችሉ ነው ብሎዋል ::
በተለይ እንደ ስራ አመራር ተቋም ያለ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በተገቢው መንገድ ተንቀሳቅሶ ውጤታማ የሚችለው በክልሉ አገልግሎቱን የሚያገኙ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ስለ ተቋሙ የጠራ ግንዛቤ መኖራቸውና በተቋሙ እቅድ ትግበራና አሰራር ላይ የጋር መግባባት በመፍጠር በጋራ መስራት ሲችሉ መሆኑን በመድረኩ ላይ አብራርተዋል ።
በውይይት መድረኩ በተቋሙ በኩል ከምስረታው እሰከ አሁን እስካለንበት ጌዜ ድረስ በስራ አመራር መስክ ስልጠና በመሥጠትና በማስተባበር ፣ በማማከርና በምርምር የሰራቸው ስራዎች ፣ እንዲሁም እነዚህን በአዋጅ የተሰጡትን ስልጣንና ኃላፊነት በመወጣት በኩል የነበሩት ተግዳሮቶችና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ለመድረኩ ተሳታፊዎች ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይቀርባል ።
እንዲሁም ከሌሎች ሴ/መ/ቤቶች ጋር የነበረው ግንኙነት ምን እንደሚመስልና ለቀጣይም ግንኙነቱን አጠናክሮ ለመስራት መፍተሔ የሚፈጥር መድረክ እንደሚሆን የሚጠበቅ ነው ።
**** መረጃው ከስራ አመራር ተቋም የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ነው ***



