የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ስራ አመራር ዋና ዳይሬክተር አቶ ዩሐንስ ተሰማ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ተቋማት ለደንበኞቻቸው የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ እና ምቹ ለማድረግ በስራ አካባቢ ካይዘንን ተግባራዊ ማድረግ እና ልምድ ማድረግ እንዳለባቸው በተቋማት መካከል የተሞክሮ ልዉዉጥ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ እንድሪስ በበኩላቸው የካይዘን ፍልስፍናው ቀጣይነትና ተከታታይነት ባለው ለውጥ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ሠራተኛውን የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ቀጣይነት ባለው ለውጥ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ከአመራሩ ቁርጠኝነት እንደሚጠበቅ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት በክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እና አሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካይዘን ትግበራዎቹ በተቋማችን አማካሪዎች ስራዎቹ እየተሰሩና እየተገባደዱ ያሉ ሲሆን በስፖርት ኮሚሽን እና ክልል ፋይናንስ ቢሮዎች ደግሞ የማጣራት ስራዎች ተጠናቀው ወደ ማደራጀት ስራ እየተሰራ እንደሚገኙ በመስክ ምልከታ ወቅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የመስክ ምልከታ በተደረገባቸው ቢሮዎች በተለይ ከክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ እና ከአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዘዳንት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የክልሉ ሥራ አመራር ተቋም የካይዘን ትግበራ እንዲከናወን በማድረግ ረገድ ከግንዛቤ ማስጨበጪያ ስልጠና ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድጋፍና ክትትል ስላደረገልን እጅጉን ምስጋና እናቀርባለን በማለት በውይይት ወቅት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዩሐንስ አክለውም ካይዘንን በቢሮ መተግበር ጥራትና ምርታመነትን ይጨምራል፣ ወጪን ይቀንሳል ፣ስራን ሰርቶ የማስረከቢያ ጊዜን ያሳጥራል፤ ተቋሙ ውጤታማ /ትርፋማ ይሆናል ፤የደንበኝነት እርካታ ከፍ ይላል ስለሆነም ተቋማችን የጀመረውን ስራ በሌሎች ተቋማትም ጭምር በስፋት የሚሰራ መሆኑን ጠቅሰው ሞዴል የካይዘን ትግበራ ማዕከሎችን በስታንዳርድ መሰረት ለይተን ተሞክሮዎችን በቀጣይ ለሌሎች ተቋማት የማሳየት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ለተጨማሪ መረጃዎች:-
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Email Address
info@bgrsmi.gov.et
Telegram Address
https://t.me/bgrsmi




















