የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም የ2015 በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተደረገ

ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ሲያከናወናቸው የነበሩ ስራዎችን ሁሉም ሠራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ::

የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም በ2015 በጀት ዓመት በ2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ሲያከናውናቸው የነበሩ ስራዎችን አፈጻፀም ሪፖርት ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች በተገኙበት ገምግሟል።

የተቋሙን የ2015 በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ረፖርት ያቀረቡት የስራ አመራር ተቋም የዕቅድና ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን ሲሆኑ 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ መሆኑን ሠራተኞቹ እንዲወያዩ አቅርቧል ::

በተያዘው ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃጸም የተሻለ ውጤት የታየበትና አፈፃፀሙ ከፍተኛ መሆኑን ሠራተኞች የገመገሙ ሲሆን ተቋሙ የስልጠና ማዕከል እንደ መሆኑ መጠን ጥናትና ምርምር ፣ የምክር አገልግሎት ፣ ስልጠና መስጠትና ማስተባበር ስራዎች የሚሰሩበት በመሆኑ ቀሪ ስራዎች እንደሚኖሩ በማመን ቀሪ ስራዎችን ለተገኙው ዕቅድ አፈፃፀም እንደግብዓት በመጠቀም ለቀጣይ ስራዎች ውጤታማ ስራ ለመስራት ጥያቄና አስተያየት በመስጠት ግምገማው ተጠናቅቋል ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *