ሥራ አመራር ተቋም (ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም. ፣ አሶሳ ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሥራ አመራር ተቋም የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርትና በቀጣይ 2016 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል */*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/////////**/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*
የተቋሙን በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርትና የበቀጣይ 2017 በጀት ዓመት መነሻ ዝርዝር ዕቅድ ትግበራ በሰነድ ያቀረቡት የተቋሙ እቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን ሲሆኑ በቀረበው እቅድ አፈጻጸም ሪፓርትና በቀጣይ 2017 በጀት ዓመት ዝርዝር መነሻ እቅድ ትግበራ ዙሪያ የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎችና መላው ሰራተኞች ተሳትፈዋል ።
በቀረበው ዕቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ላይ ሁሉም ሰራተኞች ጥልቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን እንደ ተቋም በተቋሙ አቅም ለመስራት በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ዝርዝር ተግባሮች አበረታች አፈጻጸም እንዳስመዘገቡ በእቅዱ ትግበራ ወቅት ያጋጠመው ተግዳሮቶች፣ ለተግዳሮቶቹ የተወሰደው የመፍተሄ አቅጣጫና ለአፈጻጸሙ እንደ ተግዳሮት የነበሩ የውስጥ ገቢ ችግሮች በመድረኩ በስፋት ተነስቷል ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዩሐንስ ተሰማ እንዳሉት በበጀት አመቱ ተቋሙ በእቅድ የያዛቸውን ተግባራትን ማከናወን የቻለ መሆኑን ጠቁመዉ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል እና ውስንነቶችን ደግሞ ተግባራትን በመለየት በቀጣይ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በክልሉ መንግስት በጀት የሚደገፉ በተቋሙ እየተገነቡ ያሉ የማስፋፊያ ግንባታዎች ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፣ የሰልጣኞች ማደሪያ ህንፃ ግንባታ ፣ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ጥልቅ የውሀ ጉድጓድ በተቻለ መጠን በተያዘላቸው ጊዜ ቀሪ ስራዎቹ በ2017 በጀት ዓመት ተጠቃለው እንደሚጠናቀቁና ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ በውይይት ወቅት ለተቋሙ ሰራተኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
በመጨረሻም በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ወቅት እንደ ተግዳሮት ተለይቶ የተቀመጡ ስራዎች በቀጣይ በ2017 በጀት ዓመት ዝርዝር መነሻ ዕቅድ ውስጥ ተካተው እንደሚሰራ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በሥራ አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሰራተኞች የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማትና የምስጋና ምስክር ወረቀት በማበርከት የሪፖርት ግምገማዉ ተጠናቋል ።









