ስራ አመራር ተቋም (አሶሳ ፣ህዳር 05/2016ዓ.ም )የቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም ቦርድ አባላት የ2016 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ  ዓመት  ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን  ገመገመ።

ተቋሙ በሩብ ዓመቱ በዕቅድ ይዞ ሲተገብራቸው የነበረው የስራ አፈፃፀም ምን ይመስላል በሚለው ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ የተደረገ ሲሆን ሪፖርቱን የስራ አመራር ተቋም የዕቅድና ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀይማኖት ሙሉቀን አቅርበዋል።

የስራ አመራር ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ፣ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ  ኃላፊ ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ  የቦርድ አባላት በተገኙበት የሩብ ዓመቱን አፈጻጸም ደረጃ ገምግመዋል ።

ተቋሙ በ2016 ዓ.ም በ1ኛ ሩብ ዓመት  ታቅዶ በከፍተኛ ውጤት የተከናወኑ ፣  በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጥልቀት በመወያየት ጥያቄና አስተያየት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በዕቅድ የተያዙ ተግባራቶች በተጠናከረ ና በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚተገበሩ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *