የቤ/ጉ/ክ/መ/ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የስራ አመራር ተቋም ቦርድ ስብሳቢ ለነበሩት የተከበሩ አቶ መሐመድ አብዱላዚዝ የሽኝትና የምስጋና መድረክ ላይ የክልሉ ም/ ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ቢሮ እና አዲሱ የስራ አመራር ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ለተቋሙ አዲስ ለተመደቡ የቦርድ አመራር ና ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የስራ ትውውቅ በዛሬው ዕለት አድርገዋል ።
አክለውም በቀጣይ በተቋሙ የስራ አቅጣጫዎች ላይ በቅርበት እንደሚሰሩ ተናግረው በግንባታ ላይ ያሉ መሠረት ልማቶችን ጎብኝተዋል ።
በመድረኩም የቀድሞ የክልሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የስራ አመራር ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መሐመድ አብዱላዚዝ ለአዲሱ የስራ አመራር ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት ክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የሰነድ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ከስራ አመራር ተቋም ጋር ለብዙ ዘመናት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርበት ሲሰሩ እንደነበር ለአዲሱ ቦርድ ስብሳቢና ለአዳዲስ የቦርድ አባላት ገለፃ አድርገዋል ።
በተጨማሪም ከስራ አመራር ተቋም ጋር በነበራቸው ቆይታ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን ማሻሻያዎችን ከተቋሙ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር በማፅደቅና በቅርበት ክትትልና ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር ገልጸው ለአዲሱ የተቋሙ ቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት ለክልሉ ም/ ርዕሰ መስተዳደር ና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ለሆኑት ለክቡር አቶ ጌታሁን አብዲሳ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል ።
ለተጨማሪ መረጃዎች፤
Facebook link https://www.facebook.com/profile.php?id=100054324349942
Website link
www.bgrsmi.gov.et
Gmail Account
bgrsmanagementinstitute@gmail.com
